ለባልደረባው ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ያልታመነ - አፍቃሬ ወያኔ እና የወያኔን ህልውናን ጠባቂ ግለሰብ ለነገደ አማራ ሕዝብ ህልውና በቅንነት ታግሎና አታግሎ ነጻ ያወጣናል ብዬ እራሴን የማጃጅል ሰው አይደለሁም‼️‼️‼️
- eyobabyssinia
- Jan 29
- 3 min read

ለባልደረባው ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ያልታመነ - አፍቃሬ ወያኔ እና የወያኔን ህልውናን ጠባቂ ግለሰብ ለነገደ አማራ ሕዝብ ህልውና በቅንነት ታግሎና አታግሎ ነጻ ያወጣናል ብዬ እራሴን የማጃጅል ሰው አይደለሁም‼️‼️‼️
የብ/ጄ ተፈራ ማሞ ታማኝነት ለጸረ አማራዋ ህወሃት ነው እንጂ ለአማራ እና ለአማራ ፋኖ አይደለም- አይሆንምም‼️‼️‼️
***ወንድወሰን ተክሉ***
📌 የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ማን ነው???
ጄኔራሉ ገና በአፍላ እድሜው በ 1975/76 ላይ በወቅቱ የነበረው ወጣት ደርግ፣ ኢሕአፓ፣ ኢዲዩ እና ወዘተ አይነት ድርጅቶችን ሲቀላቀል "እኔ በዚያን ግዜ የነበረቺውን ትሃትን (ወያኔን) ነው የምቀላቀለው ብዬ በ1975 ላይ ጠይቄ ነበር፣ ሆኖም ትንሽ ቆይ እድሜህ አልደረሰም ብለውኝ ለአንድ አመት ካቆዩኝ በሃላ በ1976ላይ ትሃትን ተቀላቀልኩ " ብሎ የራሱን ህይወት ታሪክ የተረከርልን ሰው ነው።
ተፈራ ማሞ በ1976 ትሃትን ሲቀላቀል ጎንደር በለሳ ላይ በ38 የኢሕአፓ ትራፊዎች እነ ታምራት ላይኔ፣በረከት ስምኦን፣አዲሱ ለገሰ፣ተፈራ ዋልዋ፣ ያሬድ ጀቤሳ፣ ህላዊ ዮሴፍ -ወዘተ በሚባሉ የኢሕአፓ አባላት የተመሰረተው ኢሕዴን ሶስተኛ አመቱን የያዘ በወያኔ የተቋቋመ ህብረ ብሄር ድርጅት ነበር። እናም ትሃት( ወያኔ) ይህንን የትግሬነት ደም ያለበትን ወጣቱን ተፈራ ማሞን ወደ ኢሕዴን አዛወረቺው። ተፈራ ማሞ አባቱ ከትግራይ እንደርታ ወደ ወሎ ቤተ አምሃራ የተጋዙ ትግሬ ሲሆኑ እናቱ ደግሞ በአባታቸው ከጎንደር በእናታቸው ከጎጃም የተወለዱ መሆናቸውን የራሱን ባዮግራፊ በጻፈው መጽሀፍ ገጽ 47 ላይ አስፍሮ አስቀምጦታል።
ወያኔ ድል ቀንታት በ. 1983 አዲስ አበባን ከተቆጣጠረች በሃላ በ2ኛው አመት ላይ የታላቁን አባታችንን ፕ/ር አስራት ወልደየስን የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ለመግታት ኢሕዴንን ብአዴን (ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ) ብላ ስሙን በመለወጥ አማራ ያልሆኑትን እነ ተፈራ ዋልዋ፣ አዲሱ ለገሰ፣ በረከት ስምኦን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ተፈራ ማሞንና መሰል None Amhara ግሳግሶችን የአማራ ሕዝብ ተወካይ ናቸው በማለት ለድፍን 27 አመታት ሕዝባችንን ስትጨፈጭፍ - ብአዴንም የተፈጠረበትን አላማን በፍጹም ታማኝነት አማራውን በመጨፍጨፍና በማስጨፍጨፍ ተግባር ላይ ተሰማርቶ እነሆ እስከዛሬ ድረስ በስልጣን ላይ ያለ ሀይል ሆነ። ተፈራ ማሞም ለዚህ ውለታው ብ/ጄ ለመሆን ቻለ።
ይህ የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ የሆነው የብ/ጄ ተፈራ ማሞ እጅግ ጭምቅ ተደርጎ በአጭር የቀረበ የፖለቲካ Background ታሪክ የሚገልጽ ሲሆን ጄ/ሉ የአማራ ልዩ ኃይል ሲመሰረት ከጀግናው ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ጋር ሆኖ በምክትል አዛዥነት ያገለገለ ከመሆኑም በላይ ጄ/ል አሳምነው ጽጌ በጸረ አማራ ኃይሎች በተገደለ ማግስት አደባባይ ላይ ብቅ ብሎ በአለቃው ጄ/ አሳምነው ጽጌ ላይ ክህደት በመፈጸም የሀሰት ምስክርነት ሰጠ ከሀዲ ሰው ነው።
ከሁሉም በላይ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ወደ ሸዋ ምድር ከገባበት እለት ጀምሮ እስከ ትናንት በስቲያ ያስተላለፋቸውን እና እያስተላለፋቸው ያሉትን መልእክቶችን ጭምቅ አድርገን ስንመለከት :-
፩ኛ- ወደ ጫካ በገባ ማግስት የአሰገድ መኮንን ክህደት በመከላከል ብቅ ብሎ ሲናገር ተደመጠ
፪ኛ- የሀምሌ ዘጠኝ 2024 አፋሕድን የመሰረተውን የምርጫ ውጤት አንቀበልም ብለው ረግጠው የወጡትን በዘመነ ካሴና በአሰግ መኮንን የሚመሩትን ኃይሎች በመደገፍ በአፋሕድ አመራር ላይ መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲያስተጋባ ተደመጠ
፫ኛ- ብልጽግና ወያኔን የሚወጋ ከሆነ ከሃላ እንከመርበታለን፣ እኛን አልፎ በምንም አይነት ተአምር ብልጽግና ወያኔን እንዲመታ አንፈቅድም በማለት Literally የአማራን ክልል ለትግራዪ ወያኔ የብልጽግናን ተዋጊ ሰራዊት የሚያሰርጉበትና የሚያስቆሙበት Buffer Zone አድርጎ ወያኔን በአማራ ሕዝብ Expense እንደሚከላከል ደጋግሞ ሲናገር ነው መስማት የቻልነው።
ይህንን አባባሉን አሁን የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ ሆኖ መመደቡን ከተነገረን በኃላም ከአፍቃሬ ህወሃቱ ጋዜጠኛ በቃል አላምረው ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ " እኛን ተራምዶ አልፎ ወያኔን የሚወጋ ካለ አንለቀውም ፣ እኛም እንወገዋለን " በማለት ሲናገር ሰምተነዋል።
በዘር ሀረጉ በአባቱ እንደርታ ትግሬ የሆነውና የፖለቲካን "ሀ'ሁ---" በትሃት ውስጥ ተምሮ ጥርሱን የነቀለው ተፈራ ማሞ የአፋብን ወታደራዊ ዋና አዛዥ ተብሎ በአነ ተመስገን ጥሩነህ ቤተሰብ በተመደበ ማግስት ትህነግ/ትሃት (ወያኔ) በጠለምት ግንባር በመቶ የሚቆጠሩ ታጣቂ ሚሊሺያዎችን በማሰማራት ጦርነት ለመክፈት በቅታለች።
በዚህ ጦርነት በርካታ የህወሃት ታጣቂ ሚሊሻ ተገድሎና ተማርኮ ትንኮሰው የከሸፈ ቢሆንም አፋብን የሚባለው ስብስብ ግን እስካሁን ድርጊቱን ፈጽሞ ሲያወግዝ አልሰማንም። በተጻራሪ ሁኔታ የአማራ ግዛቶች በጸረ አማራዋ ወያኔ ጠለምት ላይ የትንኮሳ ጦርነት በተከፈተበት ወቅት የተመስገን ጥሩነህ አጎት ልጅ የሆነውና የአፋብን ቃለ አቀባይ ነኝ እያለን በእውነተኛ ታጋዮች ላይ የግድያ ዘመቻ የከፈተው አስረስ ማረ ዳምጤ የአማራን ሚዲያዎችን ለመጠርነፍ የሚያስችል መግለጫ ሲያወጣ ነው ያየነው።
እናም ትናንት ወደ ትግል "ሀ" ብዬ የገባሁት በ 1975/76 ላይ ትሃት ተብላ ስትጠራ ከነበረቺው ወያኔ ጋር ነው ያለን ብ/ጄ ተፈራ ማሞ በዘር ሀረጉም ከትግራይ እንደርታ ከሆኑ አባት የተወለደ ትግሬ የሆነ ሰው እና Just የዛሬ ሰባት አመት በአለቃውና በባልደረባው ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ላይ ክህደት የፈጸመ ሰው፣ ዛሬም ወያኔን የሚነካ ካለ በሬሳችን ላይ ተረማምዶ እንጂ እኛ እያለን አይሆንም እያለ በሚናገረው ሰው ዋና የጦር አዛዥነት የአማራ ሕዝብ ነጻ ይወጣል ብዬ ፈጽሞ እራሴን አላታልልም። በተፈራ ማሞ የጦር አዛዥነት የአማራ ሕዝብ ነጻ ይወጣል የሚልን ቅዠት ፈጽሞ አልጋራም። የተፈራ ማሞ Political Loyalty ለወያኔ ህልውና ነው እንጂ ለነገደ አማራ ሕዝብ አይደለም።
ጃንዋሪ 17-2026 እራሱን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ብሎ የሰየመው ስብስብ - ምንም እንካን ከመስክረም ጀምሮ አንድ አማራዊ አደረጃጀትን ለመፍጠር በአፋሕድ እና በአፋብኃ መካከል ሲካሄድ የቆየ ንግግር ቢኖርም በመጨረሻዋ ሰአት ላይ ግን አንዳችም ምርጫ ሳይካሄድ የተመስገን ጥሩነህ ኤጀንት የሆነው አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ዘመነ ካሴና ጥቂት ግለሰቦች ብቻ በመደቡት የስልጣን ድልድል ባለ. 19 ፖሊት ቢሮ አባል ያለውን አመራር መርጠናል ብሎ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ቢጥርም ስብስቡ ምንም አይነት ምርጫ እንዳላደረገ በመታወቁ በእውነተኛ አማራዊያን ዘንድ ያለው ተቀባይነት ሳይወለድ የጨነገፈ ስብስብ ለመሆን በቅታል።
አዎን ትግሬ የአማራን ትግል ሊደግፍ ይችላል። ትግሬ ለአማራ ህልውና ትግል ታግሎ በማታገል ዋና የጦር አዛዥ መሆን ይችላል ብሎ አማራን ሊያሞኝ የሚዳዳው የህወሃት ካድሬ ብቻ እና ብቻ ነው። የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ከትግሬ እና ከአፍቃሬ ወያኔ ተጽእኖ ነጻ ማውጣት የመላው አማራ ሕዝብ ግዴታ ነው። አበቃሁ።



Comments