top of page
Search

የአዲስ አበባ ምክር ቤት መግለጫ ሰኔ 10፣ 2018 ዓ.ም

  • eyobabyssinia
  • Jun 17
  • 0 min read
የአዲስ አበባ ምክር ቤት መግለጫ---ሰኔ 10፣ 2018 ዓ.ም
/
ከአርሲ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ጋዜጠኞች በአገዛዙ መታሰራቸውን በጥብቅ እናወግዛለን!!!
/
ሰኔ 10፣ 2018
/
በብልጽግና አገዛዝ እና በርዕዮት አጋሩ ኦነግ/ሽኔ  ግንቦት 23/24 ቀን 2018 በምስራቅ አርሲ ሶስት ወረዳዎች በተፈጸመ አሰቃቂ የጄኖሳይድ ጥቃት፣ ከ50 በላይ ንጹሃን በግፍ መጨፍጨፋው፣ ሁለት የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አቢያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ ከ300 በላይ ቤቶች መቃጠላቸው፣ ከ190 በላይ ሰዎች ደብዛቸው መጥፋቱ እና ከ500 በላይ አባወራዎች መፈናቀላቸው በወቅቱ መገለፁ ይታወሳል።
ሆኖም፣ በቀጣይነት የተሟላውን እውነታ መሉ ለሙሉ ወደ አደባባይ ለማውጣት በተደረገ እርብርቦሽ፣ የማቾች ቁጥር በእጅጉ አሻቅቦ ከ112 በላይ ደርሷል። እውነትን የማይወደው አገዛዙ፣ ይህንን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ይፋ ለማድረግ ድምጽ የሆኑትን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እና ጋዜጠኞችን እያደነ በማፈስ እና በማሰር የተፈጸመውን አሰቃቂ ወንጀል ለመደበቅ እየተወራጨ ይገኛል።
 በዚህም መሰረት፣ እነ ቀሲስ መምህር ዶ/ር  ዘላለም መዝገቡን ጨምሮ በርካታ የኦርቶዶክስ አገልጋዮችን በግፍ ያሰረ ሲሆን፣ ሰሞኑን ደግሞ ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይከዳኝን በግፍ አፍኖ በጨለማ ቤት አስሯል። ባለፈው ሳምንት፣በኢትዮጰያ ጉዳይ ሚዛናዊ ዘገባዎችን በማቅረብ የምትታወቀውን ፈረንሳዊቷ ጋዜጠኛ ኦጋስቲን ፓስሊን በበቀል ከሀገር ማባረሩ ይታወሳል።
ቀደም ሲል የአገዛዙ ልሳኖች በሆኑት ፋና እና ዋልታ ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት ስትሰራ የነበረችው እና በአሁኑ ግዜ በግሏ የምትንቀሳቀስው ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይከዳኝ፣ በምስራቅ አርሲ የተደረገውን አሰቃቂ ጭፍጨፋን እውነታ በመዘገቧ ብቻ ሰኔ 1 ቀን 2018 በአገዛዙ ታፍና ከማንም ሰው ጋር እንዳትገናኝ ለብቸዋ ከታሰረች በኃላ(Solitary Confinement)፣ ሰኔ 9፣ 2018 ዓ.ም በእነ መምህር ዶ/ር መዝገቡ ካሳ ክስ መዝገብ ፍርድ ቤት እንደቀረበች ምክር ቤታችን ማረጋገጥ ችላል።
ድርጊቱ በንጹሀን ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋን ከፈጸመና ካስፈጸመ የጄኖሳይድ አገዛዝ የሚጠበቅ የአፈና ተግባር ቢሆንም፣ በእስር ላይ ለሚገኙት ወገኖች ድምፅ መሆን ግድ ይላል።
ንጹሀንን ጨፍጭፎ ድምጽ የሆኑትን የህብረሰብት ክፍሎች የማፈንና የማሰር ተግባሩ ዓላማ ግልጽ ነው። አገዛዙ በሕብረተሰቡ ውስጥ ፍርሃትን አስፍኖ ንጹሃን ሲጨፈጨፉ ዝምታ እንዲነግስ  ነው የፈለገው።  ይህ መቼም የማይሳካ ከንቱ ምኞት ነው።
ስለሆነም፣ በምስራቅ አርሲ በግፍ ለተጨፈጨፉት ንጹሃን ሰለባዎችን ድምጽ የማሰማቱ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤታችን የሚሰራውን ያህል፣ ይህንን ጭፍጨፋ ይፋ በማድረጋቸው ብቻ በግፍ የታሰሩትን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ጋዜጠኞችም ድምጽ በመሆን እስራቸውን በጥብቅ ያወግዛል። በዓለምአቀፍ መድረክም ድምፃቸው ይሆናል።
ስንተባበር እንጠነክራለን፣ እናሸንፋለን!!!
የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት
ሰኔ 10፣ 2018 See less

 
 
 

Comments


bottom of page