top of page
Search

ለማይቀረው ድል ተዘጋጅ !

  • eyobabyssinia
  • Feb 11
  • 1 min read

አብይ አህመድ የተባለ ጥቁር ናዚ የአማራን ህዝብ ለሶስት አመታት ያህል ሲጨፈጭፍ ከርሞ እግረኛ ሰራዊቱን ካስጨረሰ በኋላ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሲለበለብ ፈርጥጦ በለቀቃቸው ከተሞች በተለይም በዛሬው እለት በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ በድሮንና በጦር ጀት እየደበደበ ከተማዋን በማውደም ላይ ይገኛል ።በዚህ ጭፍጨፋ ሰላማዊ ዜጎችና የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሰማይ በሚወርደው የአውሮፕላን ቦንብ እየነደዱ ነው ።ይህ ለአማራ ህዝብ ከኦህዴድ ኦነግ :ከህወሓት :ከቱርክ :ከአረብ ኤምሬትስ :ከቻይና ከሩሲያና ከአዘርባጃን የተበረከተ አንድን ህዝብ የማጥፋት የቤት ሥራ አካል ነው ።


አብይና ወላጅ አባቱ ህወሃት በስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ይህ ጭፍጨፋ መልኩን እየለዋወጠ ይቀጥላል ።ዛሬ ደብረታቦር ላይ የሆነው ነገ ባህርዳር :ደሴ :ወልዲያ :ኮምቦልቻና ደብረብርሃን ላይ እንደሚሆን አምኖ ትግሉን ማጠንከርና ህዝቡን በጎበዝ አለቃ በማደራጀት ለመጫረሻው  ፍልሚያ መዘጋጀት ያስፈልጋል ።ጀግኖቻችን ወደ ከተማ ከመግባታቸው በፊት የድሮን ስምሪት ጣቢያዎችን ቀድሞው ማስወገድ ላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል ።በተረፈ አጀንዳ እየፈጠረ ሲሰዳደብ የሚለውን የአማራ ዲያስፓራ የሚያስተባብር እንደነ አርበኛ ተሾመ አበባው ራስ ደረጀ በላይ ሻለቃ መከታውና ሌሎችም እውነተኛ መሪዎች ተነጋግረው የቤት ሥራ መሰጠት አለባቸው እላለሁ ።ዲያስፖራው ከስድብ ይድናል ።ቲክቶክም ለትግሉ እገዛ ይሰጣል ።


የጠላት ክፋት የእኛን ጀግንነት ያደምቀዋል እንጂ እኛ ነፍጠኞች እንኳን ዛሬ ከ85 ዓመታት በፊትም በግራዚያኒ የመርዝ ጋዝ አልተንበረከክንም !!


ድላቸንም ነፃነታችንም ያለው በእጃችን ነወ።


ድል ለአማራ ህዘብ


ድል ለአማራ ፋኖ!


ከአዳባይ



 
 
 

Comments


bottom of page