top of page
Search

ከእንግዲህ በአማራ ሞት መንገስ የለም !

  • eyobabyssinia
  • Feb 13
  • 3 min read

ኢትዬጲያ ከምትፈርስ እኔ ልሙት እያለ ለብዙ ሺህ አመታት የታገለ የቆሰለ:አካሉ የጎደለ ቤት ንብረቱ የፈረሰና ውድ ህይወቱን እየሰዋ ዛሬ ላይ ያደረሳት አማራ በዘመናችን ተከብሮ ሊኖር ይቅርና ሰው መሆኑ እንኳን ተክዶ ጠርዝ በረገጡ የኦሮሞና የትግራይ ጎጠኞች ጥላቻ ስቃይ እየተቀበለ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ተሻገረ ።በሃገሬ ላይ የከፈልኩት ዋጋ እንኳን ቢቀር እንደ ዜጋ ሰርቼ ልኑር ቢል “አንተ እስካለህ ድረስ ቁርጥራጭ ሃገር መፍጠር አንችልም “አክሱም :ላል ይበላ:ፋሲል ወዘተ እያልክ የእኛን መንደር አላነሳህም ይልቁንም ጡት ቆርጠህ ነበር የሚል የመግደያ አጀንዳ ፈጥረው በአለም ላይ ያልተፈፀሙ የጭካኔና ተከታታይነት ያላቸው ወንጀሎች ፈፀሙበት ።ትናንት ሁሉንም ያስተማረን አማራ ነው ብለው የሬዲዬና ቴሌቪዥን መድረክ ያሞቁ የነበሩ”የህወሓት ስሪት ብሄር ብሄረሰቦች “አንዲት ቀን ለደቂቃዎች እንኳን አማራ ለምን ይገደላል ብለው ሲጠይቁ ማየት የምፅአት ያህል ርቋል።በአብዛኛው በአማራ ልሂቃን ተሳትፎ ተመስርተው በሰላሙ ጊዜ እንወክልሃለን : ድልድይ እንኳን ባይኖር ወንዝ ፈጥረን ድልድይ እንሰራልሃለን ሲል የነበሩ አስመሳይ ኢትዮጵያዊ ፓለቲከኞች ወደየሰፈራቸው ገብተው ኑሮአቸውን እየገፋ ወይ አማራው አሸንፎ እስኪመጣ ካልሆነም ጠፍቶ እስኪያልቅ አድፍጠው ይጠብቃሉ ።አለባበሱን አሳምሮ ወንጌል ልስበክ:ልዘምር እያለ የአማራን የዋህ አማኝ በየአውደ ምህረቱ ቦታ ይጠበው የነበረ የሰላም ቀን አርበኛ ሰባኪና ዘማሪ የአማራ እናቶች ህፃናትና አረጋውያን ሞት ለእሱ የስብከቱ አካል አይደሉም ።ቤተክርስቲያን ይሰራ :ልማት  ይስፋፋ ወዘተ እያሉ በአመት አንድ ጊዜ እስከ ሩብ ሚሊዮን አበል የሚከፈላቸው ጳጳሳት አማራ ሲታረድ ቀሳውስት ሲገደሉ መነኮሳት ሲደፈሩ አብያተ ክርስቲያናት በከባድ መሳሪያ ሲወድሙ ብርቅዬ ሊቃውንት እየታደኑ ሲረሸኑ እነሱ አልሰሙም ።መገበሪያ ሰፍሮ ለስጋ ወደሙ የሚቀርበውን ንፁህ ስንዴና ወይን አምርቶ የሰበካ አባልነቴ እንዳይቀር በማለት ጤፍና የቤት እንስሳቱን እየሸጠ በድህነት የሚኖረው አማራ ቢሞት ለአኛ አባቶች ዜናው አይደርሳቸውም።ዛሬ አማራ በሚኖርበት አካባቢ ብርሃኑ ጁላ መስጅድ ሲያቃጥል ለአህመዲን ጀበል ይሁን ለጣሂር መሐመድ የብልፅግናን ራዕይ እንደማሳካት ስለሆነ ቆመው ያጨበጭባሉ።አዲስ አበባ ላይ ከ ሃያ በላይ መስጅዶች ፈርሰው ህዝበ ሙስሊሙ ማምለኪያ ቦታ በማጣት አዝኖ በየቤቱ ሲቀመጥ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ወይንም ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የሚባል ካድሬ ለሚመራው መጅሊስ ዜናው አልደረሰውም ።ምክናያቱም የፈረሰውና የተቃጠለው የአማራ ንብረት እንጂ የእግዚአብሔር ወይንም የኣላህ ቤት አይደለምና ።ዘንድሮ አማራ በጦርነት ላይ ባይሆን ኖሮ 150 የሚደርስ የቅፈላ ፓለቲካ ፓርቲ አብይ አህመድን አጅቦ ዳግም ለማንገስ ይቋቋም ነበር ።አማራ በየዘመናቱ እንቢ ለሃገሬ ብሎ ከእሳት ጋር ሲፋለም ብልጣ ብልጡ የፊደል አርበኛ ከረቫት አሳምሮ ማይክ እየቀማ አጋፋሪ ሲሆን አመታትን የተሻገርን ቢሆንም ያ የሞኝነት ዘመን ማለፉን ያልተረዱ የስልጣን ርሃብተኞች ያንኑ ስልት ይዘው ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል ።በአንድ በኩል በዲያስፖራው ሸምጋይ መሰለው የፋኖን ትግል አቅመ ቢስ በማስመሰልና ተጨማሪ እድል እንዳስገኙ በመዋሸት ከአራት በላይ መንግስታት ላይ ተሳትፈው የቆሸሸ ታሪካቸውን በአማራ ፋኖ ጀግኖች ደም ተጠልለው ለመንፃት በሌላ በኩል ራሳቸውን የፓለቲካ አልፋ ኦሜጋ አድርጎ በማቅረብ ፋኖ ውስጥ ትግሉን ቅርፅ የሚያሲዝ በቂ እውቀት እንደሌለ በማስመሰል ማይክ የመንጠቅ ልምዳቸውን ለመተግበር በየአቅጣጫው እየዳከሩ ነው ።እነዚህ ትግል ጠላፊ የፓለቲካ ክሱራን የእነሱ ሚና ጎልቶ እንዲታይላቸው በደም እየመጣ ያለውን የአማራ ልጆች ድል ለመሰልቀጥ የራሳቸውን አላማ አስፈፃሚዎች ከፊት በመደርደር የመሪነት ሚና እንዲጫወቱና እነሱ የሚሉትን እንዲተገብሩ ከማመቻቸት በላይ ትናንት ስልጣን ወደ ሰሜን አይመለስም ብሎ ግንቦት ሰባት ላይ ሲያጨበጭብ የነበረውን የደህዴን ካድሬ መሳይ መኮንንን :የአማራ ታጋዬች ትግራይ ላይ ወንጀል ፈፅመዋል  ብላ የወልቃይት አማራን በዘር ማጥፋት እንዲከሰስ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ምስክርነት የሰጠችውን መአዛ መሐመድን የሚዲያ ካውንስል መሪ እንዲሁም የፀረ አማራው አብዲ ኢሌ አድናቂ የሆነውን ትንግረቱ የሚባል የብአዴን ካድሬ የቡድኑ አፈቀላጤ በማድረግ የ 1983 ዓ.ምህረትን ፀረ አማራ የለውጥ ታሪክ ደግመው ለመፃፍ ደጅ ደጁን እያዩ ይገኛሉ “በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ “ እንደሚባለው በዚህ ከላይ በተጠቀሰው የትግል ጠላፊው ሰብስብ ውስጥ አንድም አማራ ወይንም የአማራ ስነ ልቦና ያለው ፓለቲከኛ ወይንም ጋዜጠኛ የለም።የንቅናቄው መሪ ተብለው ከፊት የተሰለፉት 3 ወይንም 4 ሰዎች ከብአዴን ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ለህወሓት ቀድመው የገበሩና ወያኔ ከፊት ከሌለች ወደ አራት ኪሎ መግባት አንችልም የሚል የተሸነፈ ሥነ ልቦና ይዘው የቆሙ ፈሪ ግለሰቦች ናቸው ። ይህ በፓለቲካ የቀነጨረ በሴራ የደለበ ሰብስብ ፋኖ ከውጊያ ወጪ ምንም ግንዛቤ ሰለሌለው ካሸነፈ በኋላ ቁጥር በማመጣጠን ሰበብ ወደ ቤቱ እንሸዋለን ብሎ አቅዷል።ይሉሽን ባልሰማሽ ማለት እንደዚህ አይደል? እንዲህ አይነቱ ደካማ የሴረኞች ሰብስብ እንኳን የ70 ሚሊዮን አማራን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስ ይቅርና አንዲት አውራጃ ላይ ቢነግስ እንኳን ባለፋት 34 አመታት እንደሆነው ሁሉ አማራውን ከሳሽም ምስክርም ሆኖ ከማስፈጀት የሚመለስ አይደለም ።ዛሬ ዘመኑ ተቀይሯል ።ትግሉም ጥያቄውም ድሉም ስልጣኑም የአማራና የአማራ ልጆች እጅ ላይ እንጂ በብዙ ሺህ ማይል ርቆ ይቅርና እዛው ባህርዳር ከአጎታቸው ጋር ቢራ እየጠጡ መሪ ነኝ የሚሉት ባለ አምስት ጣት ባለቀለበቶችም የአማራን ትግል የመወሰኑ ቅንጣት አቅም የላቸውም ።ካላመንክ ባንዳዎችን ማስረሻን እያሱንና ሙሐቤን ጠይቃቸው ።በሚሊዮን የሚቆጠር የታጠቀ ፋኖ እየሞተለት ባለው የህልውና ትግል ውስጥ ገብቼ ፋኖ ሰንዳፋ ሲደርስ በድርድር ሰበብ እነግሳለሁ ብለህ ሻንጣ ያስተካከልክ በሙሉ ለቀድሞው ስህተት ንስሃ ለመግባት ተዘጋጅ።በድሉ ማግስት ገዳሙም መስጂዱም ለአማኞች ነፃ ይሆናሉና ።ከዚህ ውጪ የእንተና አማካሪ :የአቶ እከሌ ኮከብ ቆጣሪ ምናምን ብለህ ብትጋጋጥ ማሪያምን እልሃለሁ እሳት የለበሰው ነፍጠኛው ፋኖ ህይወቱን የገበረበትን :የእናት አባቱን ህይወት ሃብትና ንብረት ያጣበትን የነፃነት ትግል አሳልፎ የሚሰጥበት የንፋስ መግቢያ እንኳን ጭላንጭል አታገኝምና አትድከም ።አማራ ጠብመንጃ ተሸክሞ እየተዋጋ ለጩልሌዎች የሚያስረክበው ስልጣን የለም ።ፋኖ ይተኩሳል ።ያሸንፋል ።ይነግሳል ።


ከእንግዲህ በአማራ ሞት የሚነግስ ሴረኛ አይኖርም !!!



አበቃሁ


ትግሉም ድሉም የፋኖ ነው !


ከአዳባይ


የካቲት 5/2018



 
 
 

Comments


bottom of page