የወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንቅስቃሴ እና የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል
የወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንቅስቃሴ እና የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል
የአሁኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ምህዳር በከፍተኛ ውስብስብነት፣ በመዋቅራዊ ውጥረት እና በተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች መጋጨት ውስጥ ይገኛል። በሀገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ጎልተው የሚታዩትን የሶስቱን ዋና ዋና ወገኖች አቋም፣ የትግል አቅጣጫ እና በተለይም የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ፦
1. የመሪ ለውጥ ፈላጊ ኦሮሞዎች(Jawar Mohammed)
በኦሮሞ ፖለቲካ ተሳታፊዎች ዘንድ የሚታየው ዋነኛ እንቅስቃሴ በስርዓቱ ላይ ሙሉ በሙሉ ተቃውሞ ከማሳየት ይልቅ በመሪው ላይ ያተኮረ ነው። የወቅቱን የመንግስት መሪ አብይ አህመድን "የኦሮሞን ብሔራዊ ጥቅም በሚገባ አያስከብርም" በሚል ኦሮሞነታቸውን ይጠራጠራሉ። ስለዚህ አሁን ያለው ህገ-መንግስታዊ መዋቅር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የኦሮሞን ጥቅም በተሻለ ሁኔታ የሚያስከብር ሌላ መሪ በመተካት የመንግስት/የመሪ ለውጥ ማድረግ ይፈልጋሉ።
2. የመንግስት ለውጥ ፈላጊ
የህውሃት/የትግራይ ኃይሎች ፍላጎት እና የጂኦ-ፖለቲካ ሴራ
ህውሃት ሳያስበው እና ሳይዘጋጅበት ማዕከላዊ የመንግስት ስልጣኑን አስረክቦ በመውጣቱ የመንግስት ለውጥ ይፈልጋል። ሆኖም ግን የስርዓቱ እና የህገ-መንግስቱ መሰረት እንዳይነካ፣ ሁሉም ነገር ቀደም ሲል በነበረበት ሁኔታ እንዲቀጥል ይሻል።
በተለይም ህውሃት አማራ በፋኖ መደራጀቱ ትልቅ ስጋት ሆኖበታል። አማራ ጠንክሮ ከተደራጀ ወልቃይትን እና ራያን ከአማራ ቀምቶ መውሰድ እንደማይቻል ስለሚያውቅ፣ "ፅምዶ" በሚል ስም ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከሱማሌ ጋር የፈጠረውን ጥምረት ውስጥ ፋኖንም ለማስገባት ጥረት እያደረገ ይገኛል። በዚህ ሴራ ውስጥ የሱዳን፣ የሱማሌ እና የግብፅ እጅ አለበት፤ ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በኢትዮጵያ ሰላም መደፍረስ እና በደካማ ኢትዮጵያ መኖር ተጠቃሚ ነን ብለው ስለሚያስቡ ህውሃትን ይረዱታል።
ህውሃት የምስራቅ አፍሪካን ቀጠና በማመስ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ ይሞክራል። ከቀጠናው ልዩ ጥቅም ያላቸው ሀገራት ለራሳቸው ሲሉ እንዲረዱት በማድረግ፦
• ከቻለ ያጣውን የመንግስትነት ስልጣን ማስመለስ፣
• ካልቻለ ወልቃይትን እና ራያን ይዞ መገንጠል፣
• ይህም ካልተሳካ የስልጣን ሀይሉን አስጠብቆ ለመደራደር ይፈልጋል።
በዚህም "የጋራ ጠላትን በጋራ መምታት" በሚል የተጭበረበረ ሀሳብ ፋኖን ወደ ጥምረቱ ለማስገባት እየሰራ ነው። በውስጥ መረጃ እንደሚሰማው፣ ህውሃት "አብይ ከወደቀ በኋላ ቀጣይ የኢትዮጵያ መሪ አንተን እናደርጋለን" በሚል ተስፋ የፋኖን መሪ ዘመነ ካሴን መቀሌ እንዲገባ አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት እና ዮናይትድ ስቴትስ ህውሃትን ከአብይ ጋር ለማደራደር እየሰሩ እንደሆነ ይሰማል። ህውሃት ተደራድሮ ወደ ስርዓቱ ከገባ ትጥቅ እንዲፈታ መደረጉ ግልፅ ነው። ነገር ግን ህውሃት ትጥቅ ፈቶ ፋኖ ሳይፈታ ቢቀር ለህውሃት ትልቅ ስጋት እንደሚሆን ስላወቁ፣ ፋኖን ከህውሃት ጋር ደርቦ የማደራደር እና የአማራን ህዝብ ትግል የመበተን ስልታዊ ሴራ ህውሃት እየሰራች ትገኛለች።
3. የስርዓት ለውጥ ፈላጊው አማራ እና ቀጣይ የትግል አቅጣጫ
ከህውሃት ጀምሮ እስካሁን ባለው የመንግስት መዋቅር በአማራው ላይ በሲስተማቲክ እና በመንግስታዊ ደረጃ የዘር ማጥፋት፣ ማፈናቀል እና በደል ስለተፈጸመበት፣ አማራው የሚፈልገው የመሪ ለውጥ ሳይሆን ስር-ነቀል የስርዓት ለውጥ ነው!
የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎቻችን መሰረታዊ እና የህልውና ጉዳዮች ናቸው። በመሆኑም፦
• የአማራ ህዝብ በዘመነ ካሴ በኩል ህውሃት የጠለፈችውን የፋኖ አመራርነት በፍጥነት ማስወገድ አለበት።
• የህውሃትን እና የውጭ ኃይሎችን የተጭበረበረ ሴራ በመንቃት፣ የፋኖን ትግል በተገቢው መንገድ ማፋፋም ያስፈልጋል።
• ትግሉ አላስፈላጊ በሆኑ ድድርድሮች እና ጥምረቶች ሳይጠለፍ፣ ለህዝባችን ሙሉ ህልውና፣ ለማንነታችን መከበር እና ለስርዓት ለውጥ እስከ መጨረሻው መታገል አለበት እላለሁ።
✍️✍️✍️ አቶ በረከት




Comments