Stop_Using_Wrong_Equivalence
- eyobabyssinia
- Jan 26
- 3 min read

ስለአፋብን የማታውቁትን እናውቃለን እያላችሁ በሕዝባችን ላይ ለመጫን የምታደርጉትን መጋጋጥ አቁሙ-!!!!
*** ወንድወሰን ተክሉ***
📌 " አፋብንን የማይቀበል ገደል ይግባ " ሸመልስ አበራ ጆሮ
"አፋብን ሁሉም የፋኖ አመራሮች በተስማሙበት ምርጫ መሪዎቹን መርጦ እራሱን ያስተዋወቀ ድርጅት ነው" ሀብታሙ አያሌው
ሁለቱ የሚዲያ ሰዎች ሀብታሙ እና ሽመልስ አዲሱን የአፋብንን ድርጅት ሕዝባችን ሳያላምጥ እንዲውጥ እጅግ በርትተው እየጎተጎቱ ነው። ሁለቱ ግለሰቦች አይደለም አፋብን አማራን ይታደጋል ብለው ማመን ይቅርና ሳጥናኤል ያድናል ብለው ማመን መብታቸው ነው። በግላቸው ሳጥናኤን ማምለክ መብታቸው ነው። እነሱ አምነው ያመለኩትን ሁሉ እውነተኛ አዳኝ ነው ብሎ ለመስበክ መቃጣት ግን ኃጢአትም ወንጀልም ነው።
ሁለቱ ግለሰቦች በጭፍን እንቀበል ዘንድ ሊጭኑን የሚጋጋጡለት አፋብን ማን ነው?!?
ድርጅታዊ መሪውን እና 19ኙን የፖሊት ቢሮ አባላትን ምርጫ አካሂዶ ነው የመረጠው ????
ሁሉንም አውቃለሁ ባዩ ሀብታሙ አያሌው አፋብን ምርጫ አካሂዶ መሪውን አርበኛ ዘመነ ካሴን በአብላጫ ድምጽ የመረጠ ድርጅት አድርጎ ለመሸጥ እጅግ ሲጋጋጥ እነሆ ዘጠኝ ቀናትን ቆጥረናል።
ለመሆኑ አፋብን ምርጫ የሚባል ነገር አካሂዳልን ???ብለን ሀብታሙን ብንጠይቀው እኔ የምነግራችሁን እመኑ እያለ ድርቅ ብሎ ከመለፈፍ ባሻገር አንድም የአፋብንን አመራር ጠርቶ በዚህ ጉዳይ ላይ በመጠየቅ መልስ ለመስጠት ሲሞክር አላየንም። ከእሱ ይልቅ የግንቦት ሰባቱ ድምጽ መሳይ መኮንን ቢያንስ ሶስቱን የአፋብን አመራሮችን - ማለትም አርበኛ መከታው ማሞ፣ አርበኛ ጌታ አስራደንና የተመስገን ጥሪነህ ቀኝ እጅ የሆነውን አስረስ ማረ ዳምጤን አቅርቦ በማነጋገር ስለአፋብን አመራሮቹ መንገር የፈለጉትን እንዲነግሩን አድርጋል።
የኢትዮ- ሰገነቱ ሀብታሙ አያሌው ግን አንዱንም አመራር አቅርቦ ሳያነጋግር "ከፈረሱ አፍ እንዲሉ እኔ ሁሉንም አነጋግሬ የሰማሁትን ነው የምነግራችሁ ዝም ብላችሁ የምላችሁን ተቀበሉ" እያለ ሲገግምና ሲማዘዝ ነው እያየን ያለነው።
ለምንድነው ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ደረጀ ሀብተወልድ (ሌላኛው የፖለቲካ አስተሳሰብ ድሀ) ከእስክንድር ጋር ተነጋገርኩ ብሎ የጻፈው እውነት ነው ብሎ ሀብታሙ ከመናገር ይልቅ በቀጥታ አርበኛውን ኢንተርቪው አድርጎ ድምጹን የማያሰማን???
ለመሆኑ ሀብታሙ አያሌው ለመጨረሻ ግዜ ታላቁን አርበኛ እስክንድር ነጋን ኢንተርቪው ያደረገው መቼ እንደሆነ ታውቃላችሁ???
It has been so long
እጅግ ቆይቷል. አርበኛውን ኢንተርቪው ካደረገ እጅግ ቆይታል።
ነገር ግን ሀብታሙ Almost በየእለቱ አብሮ እንደሚነጋገር አድርጎ እስክንድር በዚህ ድርጅት ምርጫ ላይ አልሳተፍም ብሎኛል እያለ ሲቀደድ እንሰማለን።
ለመሆኑ የአፋብን ፖሊት ቢሮ አመራሮችን ለመምረጥ ምርጫ ተካሂዶ ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ በምርጫው አልሳተፍም ብሎ ነው እንዴ የቀረው??? ምን የተካሄደ ምርጫ አለ?!?
ሀብታሙ አያሌው እውነተኛ ጋዜጠኛ ቢሆን ኖሮ:-
፩ኛ- አፋብን ለምንድነው ምርጫ ያላካሄደው
፪ኛ- አፋብን ለምንድነው የስልጣን ድልድልን ምደባ የመረጠው ???
፫ኛ- አፋብን ለምንድነው 19ኙን የፖሊት ቢሮ አባላትን ምደባ ለአባላቱ ሳያሳውቅ ሊያውጅ የቻለው ????
፬ኛ- ለመሆኑ ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ አፋብን የሰጠህን ስልጣን የሰማህው ከሚዲያ ነው ወይንስ በግል ቀድመው ነግረውህ ነበር ???
- ቀድመው ነግረውህ ከነበረ የተሰጠህን ስልጣን እሺ ብለህ ተቀብለህ ነበር??
- እሺ ብለህ ከተቀበልክ ለምንድነው ኃላፊነቱን አልቀበልም ያልከው ???
፭ኛ- አርበኛ ዘመነ ካሴ የአፋብን ሰብሳቢ ሲባል ከማን ጋር ተወዳድሮና አሸንፎ ነው ሰብሳቢ የተባለው ?!?
-ሁለተኛ የወጣውስ እጩ አመራር ማን ነው?? በምን ያህል ድምጽ ብልጫ ነው ተበልጦ የተሸነፈው??? እና መሰል የሆኑ ቁልፍ ጥያቄዎችን ይዞ የአፋብንን አመራር እና ብሎም ታላቁን አርበኛ እስክንድር ነጋን እየጠየቀ ምላሽ ይዞልን ይቀርብ ነበር። ነገር ግን እየሆነ ያለው ከዚህ በተቃራኒ ነው።
አፋብን ተመሰረተ ከተባለበት እለት ጀምሮ ሀብታሙ አያሌው አንድም የአፋብን አመራርም ሆነ አንድም ሽማግሌ አባል አቅርቦ ሳያነጋግር ስለአፋብን A-Z የማውቅ ነኝ እያለ ደጋግሞ ሲናገር ነው እየሰማን ያለነው።
እጅግ ከገረመኝና ካሳቀኝ ስብከቶቹ ውስጥ ስለአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተናገረው ነው።
በትናንትና ፕሮግራሙ Just out of the blue የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ሲመሰረት 30 ያህል አባላት ብቻ ነበሩት። ከእነዚህም ውስጥ 10 ያህሉ ብቻ የታጠቁ ሲሆን የተቀረው ግን ጀሌ ነበር ብሎ በድፍረት ሲናገር ሀብታሙ አያሌው እታች ምድር ላይ ሆኖ የህዝባዊ ግንባሩን አባላት ቆጥሮ ያወቀ ይመስል ነበር። Very shameful
የሕዝባዊ ግንባሩን ተዋጊ አባላትን ቁጥር ዛሬ - በሀሰት ዛሬ ላይ መግለጽ የፈለገበት ምክንያት ምንድነው ብለን ብንጠይቅ የምንገኘው መልስ ንጽጽሮሽ ሆኖ እናገኘዋለን። ታላቁን አርበኛ እስክንድር ነጋን ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ጋር አነጻጽሮ ዘመነን ከፍ ለማድረግ ሲል ያመጣው ሀሰት ትርክት መሆኑን ነው ማየት የቻልነው።
ሕዝባዊ ግንባሩ አስር ያህል የታጠቁና ሃያ ያህል ተከታይ ጀሌዎችን ይዞ ነው የተመሰረተው ብሎ በገለጸበት ቅጽፈት አርበኛ ዘመነ ካሴ ግን ወሎ ላይ ዘምቶ ያደረገውን ተጋድሎ እያለ ሲቀደድ የሰማነው የሕዝባዊ ግንባሩን ስም በሀሰት የጠራበት ምክንያት ለከንቱ ንጽጽሮሽ False Equivalence ለመፍጠር እንደሆነ ነው መረዳት የቻልነው።
Dear ሀብታሙ አያሌው አፍራሳ Stop Using Wrong Equivalence-!!!!!!!!!!!!!!
አንተ አፋብን ያድናል፣ ነጻ ያወጣናል ማለት ይቅርና ሳጥናኤል ያድናል፣ ሳጥናእል ጌታ ነው ማለት መብትህ ነው። የግል እምነትህን በሕዝብ ላይ በሀሰሰት ለመጫን መጋጋጥ ግን ሀጢያትም ወንጀልም ነው። እናም አቁም። አቁሙ!!!!
አንተም ሆንክ አርቲስት ሽመልስ አበራ የሕዝብን ጥያቄ ይዛችሁ መልስ ለማግኘት የአፋብንን አመራር እያቀራባችሁ ጠይቁ፣ አነጋግሩ። እስከዛሬዋ እለት ድረስ አንድም የአፋብን አመራር አቅርባችሁ ስትጠይቁ አላየንም። ግን እራሳችሁን እንደ የአፋብን ጋዳ ጎድጋዳ አዋቂ አድርጋችሁ የምንላችሁ እውነት ነውና ሳታላምጡ ዋጡት፣ የምንሰጣችሁን ተቀበሉ፣ የምንጭንባችሁን ጸጥ እረጭ ብላችሁ ተጫኑልን እያላችሁ ነው ያለው። That is absolutely Nonsense!!!!!



Comments