top of page
Search

አንዳንድ ጉዳዬች!

  • eyobabyssinia
  • Feb 4
  • 4 min read

Updated: Feb 12


የአማራ የህልውና ትግል በይፋ ከተጀመረ እነሆ ወደ ሶስት አመታት ተጠጋ።አማራ እንደ አለው የህዝብ ብዛት (በኢትዮጵያ በቁጥር አንደኛ መሆኑ ይሰመርበት ) በተፈጥሮ የተሰጠው ጀግንነት :አልበገር ባይነትና የአሸናፊነት ሥነ ልቦና አንፃር ግራና ቀኙን ለይቶ በማያውቀው ብርሃኑ ጁላ እየተላከ የሚገባውን የዬኒፎርም ብቻ  ወታደር በስድስት ወራት ውስጥ መደምሰስ እንደሚችል ሰለምንረዳ ድላችን ዘግይቷል እያልን እንቋጫለን ።በአንድ በኩል ከላይ የተገለፁት ወሳኝ የማሸነፊያ አቅሞች በሌላ በኩል አማራ በኢኮኖሚ በፓለቲካ በባህል በሃይማኖትና በሥነ ልቦና ጫናዎች ከ ሃምሣ አመታት በላይ ስለቆየ ረጅም ጦርነቶችን መሸከም አይኖርበትም ከሚል የመቆጨት ሰሜት ጋር የሚገናኝ እውነተኛ እሳቤ ነው ።ይሁንና እንደ ማህበረሰብ ከደረሰበት በደል በላይ አማራን በአማራ ለማጋደል በተሰራው የቆየ ሴራ ምክንያት ሁሉንም የሰው ሃይልና ቁሳቁስ ወደ ትግሉ በማዞር ለማቀናጀት የወሰደው ጊዜ ከውጊያው በላይ ሌላ የውጊያ  ግንባር ነው ሊባል ይችላል ።በመንግስቱ ሃይለማርያምና አጋሮቹ ከ 200 በላይ በሆኑ የአማራ ብርቅዬ ምሁራን መገደል የተጀመረው አማራን በቋሚነት የማጥፋት እንቅስቃሴ መለስ ዜናዊን አስከትሎ አብይ አህመድ እስከሚባል ጥቁር ናዚ ድረስ አማራን የማጥፋት ሥራው የቀጠለ በመሆኑ ይባስ ብሎ ዘመናዊ ከርሳሞች ከአማራው መሐል በቅለው በጥቂት ፍርፋሪ ሰልጣንና ብልጭልጭ ኑሮ  እየተገዙ የወጡበትን ማህበረሰብ መልሰው ለመግደል ወዶ ገብ በመሆናቸው ትግሉ በተፈለገው ፍጥነት ወደ ድል እንዳይሸጋገር እንቅፋት ሆኖበታል ።በመግቢያዬ ላይ እንደጠቃቀስኩት አማራ የዳበረ የአሸናፊነት ሥነ ልቦና ያለው ለጠላት የማይንበረከክ ማህበረሰብ በመሆኑ እንጂ ደክሞ ለፍሬ ያበቃቸውን ምሁራንና የለውጥ ሃይሎች በየጊዜው እንደ መነጠቁ :ስደት መፈናቀልና አሰቃቂ ግድያ እንደተፈፀመበት ህዝብ በቀላሉ ሸብረክ የሚል ቢሆን ኖሮ በደርግ ዘመን የተፈፀመው ብቻ ወደ ነበር ታሪክነት ይቀይረው ነበር ።በደርግ ከመረሸን  የተረፋና ለታሪክ ነጋሪ በየጉራንጉሩ የተደበቁትም  ምሁራን ቢሆኑም ከፊሎቹ “ከመሞት መሰንበት” በሚል ፍርሃት ተሸንፈው ራሳቸውን ሲደብቁ ለውጥ መጣ ብለው ወደ ወያኔና ኢህዴግ የተቀላቀሉትም በየተራ እየተበሉ አልቀው ዛሬ ላሉት ብኤዴናወያን ተረፈ ሰብእ (ሰው መሳይ አጎብዳጆች) እጅ ላይ ኩሩው አማራ ወደቀ።መንግስቱ ሃይለማርያም አማራ የቆረቆራቸውን ከተሞች በከተማና ትርፍ ቤት አዋጅ 47/1967 በመውረስ “ፊውዳል “የሚለውን አማራ አንዲት ሳሎን ብቻ በማስቀረት(ኩሽናና መታጠቢያ ቤቶችም በትርፍነት ተወርሰዋል) ሙልጭ አድርጎ በመዝረፍ አማራን በቋሚነት የማደኸዬት ሥራ አስጀምሮ ለመለስ ዜናዊ አስረክበው ።የገጠሩ አርሶ አደር በደርግ ቡርዣው በወያኔ ቢሮክራት እየተባለ በይዞታው ሥር የነበሩ መሬቶችን በሙሉ በመቀማት እንደ መቃብር ቦታ በገመድ እየተለካች ለዛውም ከቀድሞው ሥርዓት ጋር ንክኪ አለው የለውም እየተባለ ተቀንጭባ ተሰጠችው ።ከራሱ የአመት ቀለብ አልፎ ከተሜውን በእህል ምርት የሚያጥለቀልቀው የአማራ ጠንካራ አርሶ አደር ያችኑ ቁራሽ መሬት ለማረስ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ከእኛ ግዛ እያሉ በሰኔ አብድረው በጥር ምርቱን በሙሉ ለእዳው መክፈያ ብለው እየተረከቡ ደሃ ህዝብ አደረጉት ።የቀን ሥራ ፍለጋ ከተማ ሲገባ ደግሞ ለማኝ የሚል ስም ሰጥተው አባረሩት። የማዳበሪያ እዳውን በጥር ካልከፈለ ደግሞ በቤት ውስጥ ያሉትን የቀንድ ከብቶች ያሸጡታል ።ልጆቹን አብልቶ ማደር ሲያቅተው ወደ አረብ ሃገራት እንዲልክ ራሳቸው ገዥዎቹ አዛኝ መሰለው ይቀሰቅሳሉ ።ልጆቹን ለመላክ ደግሞ ወይ ከካድሬ ይበደራል ካልሆነም ቀሪ ከብቶቹን ሸጦ ልጆቹን ወደ አረብ ሃገር ሲልክ ራሳቸው ደላላና አሻጋሪ ሆነው ሙሉ ሃብቱን ልጆቹንና ቅርሱን ዘርፈው ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል አማራ እንዲፈጠር ተግተው ሰሩበት።ዛሬ ሚሊሻ አድማ ብተና ካድሬ የሚባለው በሙሉና እንደ እያሱ አባተ :ማስረሻ ሰጤ ፀዳሉ ደሴና ሌሎችም ከአማራ ማህፀን ተወልደው የጨነገፉ ባንዳዎች የወጡት በዚህ የዘመናት አማራን በሁሉም ዘርፍ የመግደያ ስልት መሰረት እንጥፍጣፊ የአማራነት ሥነ ልቦና አጥተው ነው ።ለዚህ ሳይሆን ይቀራል አማራ የጎታ ልብሱ ስሙ ደረባ ፈሪን መግደል ነው ዘሩ እንዳይረባ ።ያለው  : አማራ ከመንግሥት መዋቅር ተለቅሞ እንዲወጣ በ1987 ዓ.ም  በወያኔ በተፃፈው የዲሞክራታይዜሸን ቢጫ ሰንድ ላይ እንዲህ የሚል አረፍተ ነገር ሰፍሯል”የሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ቁጥር እስኪመጣጠን ድረስ ለአማራ ብሄር ተወላጆች የሥራ ቅጥር አይከናወንም “(በተወሰነ መልኩ አባባሉን አስተካክዬዋለሁ) ይላል ።ይህ መፅሔት የሚመስል ሰነድ በመለስ ዜናዊና በበረከት ስምኦን ተዘጋጅቶ በሁሉም መንግስት መሥሪያ ቤቶች የተበተነ መመሪያ ጭምር ነበር።በገጠር የአማራን አርሶ አደር ለማስጎንበስ ደግሞ በ 1984 ዓ.ም ወደ አመራ ክልል (በወያኔ አጠራር )  አንድ መንደር ባልሳሳት ወደ ራያ አካባቢ ይመሰለኛል (ቪዲዎውን ማግኘት ይቻላል ) በሄሊኮፕተር የተጓዙት መለስ እና አዲሱ ለገሰ ከአርሶ አደር ታጋዬቹ “ሰልጣን ስትይዙ እኛን እራሳችሁን “ለሚለው ወቀሳ ሲመልስ መለስ እንዲህ አላቸው “አሁን ደርግን ተዋግተን አሸንፈነዋል የቀረን ቢሮክራሲው (የህዝብ አገልጋዬን ለማለት ነው)  ማሸነፍ ነው ።ይህ ቀላል አይደለም በዘመናት የተገነባ ስለሆነ በሂደት መሆን አለበት እናንተ ከታች እኛ ከላይ ሆነን መሐል እንደፈጥጠዋለን” የሚል አማራን አማራው እያጠፋው እንዲመጣ በአደባባይ የተነገረው እየሆነ ሰለመጣ ነው ድላችን የራቀው እልሃለሁ ።የሚገርመው በዚሁ በ1984ዓ.ም ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ የሄደው የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር (ከተሳሳትኩ እርሙልኝ)ታምራት ላይኔ ከወቅቱ የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት ሃሰን አሊ ጋር ዛፍ ሥር ቆመው “ሸርጣም ምና ምን እያለ የሰደበህን ነፍጠኛ ልኩን አሳየው”ብሎ የአማራን መገደል በአደባባይ እውቅና የተሰጠውና እየሞትን እየተሳደድን የእምነት ተቋማት የቤተክርስቲያን እና የመስጅድ አገልጋዬች እየተገደሉ ዋኖቻችንን እያጣን ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚያንደረድሩን ጥቃቶች በሙሉ በደንብ በተጠና ሴራ መሆኑን አማራ ደጋግሞ ማስታወስ ይኖርበታል ።


ደርግም ወያኔም የኮሌጅ መግቢያና የሥርዓት ትምህርት መቀየሪያ ቤተ ሙከራ አማራና የአማራ የሆኑ እሴቶች ላይ ነው ።የአማርኛ ቋንቋ እየተዳከመ ሥርአቱም እንዲዛባ የተደረገው በስህተት ሳይሆን በሰሌት ነው ።ዛሬ ላይ የአራዳ ቋንቋ እየመሰሉ በንግግር መሐልና በፅሁፍ የተሰነቀሩት ፊዳላት:ቃላትና አባባሎች የቋንቋ እድገት ከመሰለን ተሸውደናል።ጥቂት ምሳሌዎችን ለማንሳት ያህል


-ጀለስ የሚባል ቃል የእንግሊዝኛ ቃል ሲሆን ቀጥታ ትርጉሙ ምቀኛ ቢሆንም በአራዳኛ ተብሎ ወዳጅ ጓደኛ የሚል የተዛባ ውክልና ይዞ የከተማ አማርኛ ሆኖ ተከስቷል ።


-ው እና ሁ አሁን አሁን በሚዲያዎች ጭምር እየተንፀባረቀ ያለ ፀረ “ነግሬዋለሁ “በማለት ፈንታ ነግሬዋለው።አይቻለው።እመጣለው።ወዘተ


-ምን ቢለው ጥሩ ነው።ይቺማ አባባል ከሚዲያው አልፋ ቤተክርስቲያን ጭምር ደርሳለች ።ተናጋሪውም ጠያቂውም ራሱ የሚሆነበት አነጋገር ።እነዚህ ለናሙና እንጂ በአማርኛ ላይ በከፍተኛ ትምህርት እንዳይሰጥ ከማድረግ ባሻገር የግዕዝ ቋንቋና የሐይማኖት ሊቃውንቱን ጭምር እያደኑ መግደል ቋንቋውንም እምነቱንም:ታሪኩንም አብሮ የመግደልን መሰረት አልባ (baseless ) አመራን የመፍጠር በጀት ተመድቦለት የሚከወን ተግባር ነው ።አብይ አህመድ ዶሮ ሸንኩርት ብቻ ነው ።ጤፍን መመገብ ጥቅም የለውም ሲል አደነች አበቤ አረቄ እንዳይሸጥ ስትከለክል ።ፈይሳ ሌሊሳ አማርኛ የወፍ ቋንቋ ነው ሲልህ።ሽመልስ አብዲሳ ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ ሃይማኖቶች ብሎ ክርስትናንም እስልምናንም ሲያጣጥል አማራን በባህሉ በቋንቋው በእምነቱና በሥነ ልቦናው ጭምር አድቅቆ ለማጥፋት የተደገሰውን እያሰቡ ሁሉንም ለማስመለስ ጠንክሮ መሥራት ላይ አተኩረን እንታገል እያልኩ ነው ።


ዛሬ ላይ በመንግቱ ሃይለማርያም እና በመለስ ዜናዊ አንባገነን አገዛዞች ጥላ ሥር ያደገ ታጋይ ነኝ ባይ ወይንም ካድሬ ተስፋ ቢቆርጥ አትፍረድበት ።ከቻልክ የአፄ ቴዎድሮስን ሃገር ሰሪነት:የንጉስ ላል ይበላን የሥነ ህንፃ ጥበብ :የበላይ ዘለቀን ጀግንነት :የአፄ ዘርዓያዕቆብን ፍልስፍና የእምዬ ምንሊክንን እርህራሄና ሰበአዊነት የእቴጌ ጣይቱን የአመራር ጥብብ ወዘተ እየነገርከው ዘመን ተሻገሪ ታረክ ፅፎ እንዲያልፍ አበረታታው ።የአንድ ወይንም የጥቂት ቅርብ አዳሪዎች መንፈራገጥ የሰባ ሚሊዮን አማራን ህልውና ሊለውጥ እንደማይችል ባህር ከሆነው የአያት ቅድመ አያቶቸህን ጀግንነት እየቀዳህ አጠጣው ።ትናንት በእነ አስማረ ዳኘ ኘሮፌሰር አስራት ጀነራል አሳምነው እሸቴ ሞገስ ጎቤ መልኬ አሰቻለው ደሴ ናሁሰናይና በርካታ ብርቅዬ የአማራ ጀግኖች ስለአማራ ህዝብ ክብር ሲሉ መተኪያ አልባ ህይወታቸውን በክብር አሳልፈው እንደሰጡ ተረድቶ ለበለጠ ክብር እንዲዘጋጅ አበርታው ።አብረህ ለመውደቅ ተስማማ።ያን ጊዜ ጠላትህ ቀድሞ ይሸነፋል።


ለዛሬ በአርበኛ እስክንድር አባባል ልሰናበት


“አማራ ታሪኩን ያድሳል “!!



ከአዳባይ


ጥር 26/2018



 
 
 

Comments


bottom of page